የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የተበዳሪው/ የመያዣሰጪው ስም
|
የንብረት አድራሻ
|
የንብረት ዝርዝር
|
የቦታ ስፋት (ሄክታር)
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)
|
የጨረታ ሁኔታ
|
የጨረታ ደረጃ
|
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
ማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር
|
ጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መ፣ ማጃንግ ዞን፣ መንገሺ ወረዳ፣ አሽኔና ባያ ቀበሌ
|
የመስኖ እርሻ እና ግንባታዎች፣ የእርሻ ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ 145ሄክታር ላይ የተተከለ የሙዝ ቋሚ ተክል ያለው |
1000 ሄክታር በሊዝ የተገኘ መሬት
|
375,513,976.00
|
ዝግ
|
የመጀመሪያ
|
ግንቦት 25 ቀን 2017ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል።
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- አንዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች የጉምሩከ ቀረጥና ታከስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
- የድርጅቱ የስራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ ያልተሰበሰበ ወይም በክምችት ላይ ያለ የሙዝ ምርት በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል።
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊው የድርጅቱን ቋሚ ሰራተኞች በሙሉ ከመብትና ጥቅማቸው ጋር መረከብ ይጠበቅበታል።
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
