የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን CCTV Data Center Equipment Camera Surveillance System በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
CCTV Data Center Equipment Camera
Surveillance System NCB 0013/2017
ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB-0013/2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን CCTV Data Center Equipment Camera Surveillance System በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 10,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋና የቴክኒክ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልከ ቁጥር 0115172521 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
