የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፤ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራች:-
1ኛ. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የ2017 ዓ/ም ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2ኛ. ተጫራቾች የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዘጋቢ የሆነና ፤ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፍከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3ኛ. ተጫራች ዓመታዊ ሥራ ግብር የከፈለበትን ማስረጃ /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችል።
4ኛ. ተጫራች ከዚህ በፊት በዘርፉ ዕቃ ያቀረበበት ሕጋዊ ሥራ ልማድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
5ኛ. ተጫራች የአቅራቢነት ምስክር ወርቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡
6ኛ. ተጫራች በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ሰነዶች ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለብቻ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም ቢሮው ባዘጋጀው ጨረታ ሠነድ ላይ በሚነበብ ጽሑፍ በሙሙላት የድርጅቱን ስም ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በማቅረብ ለዚሁ ጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7ኛ. ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ጨረታው አየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ፣ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
8ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ስትሞሉ መ/ቤት ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት። ካልሆነ ውድቅ ይደርጋል።
9ኛ. ተጫራቾች አሸናፊ ድርጅት የአሸነፉበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ውል ማስከበርያ ከጠቅላላው ዕቃ ዋጋ 10% CPO በኮሚሽኑ ስም በማስያዝ በ3 ቀን ውስጥ ውል መግባት አለበት።
10ኛ. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ቤንች ሻኮ ዞን ጉራፋርዳ ወረዳ ድረስ ማስገባት አለበት።
11ኛ. ተጫራች ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም ።
12ኛ. ተጫራች የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
13ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በመ/ቤቱ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ CPO /ጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት 1000521691305 ላይ ገቢ በማድረግ ባንክ አድባይስ ስታመጡ በ/ደ/ም/ኤ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመምጣት መግባት ትችላላችሁ፡፡
15ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
