በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት (በገ/ጉ/ወ) ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለአዚት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የላብራቶሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/27/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት (በገ/ጉ/ወ) ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለአዚት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የላብራቶሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ተጫርተው ከሻነፉ በኃላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጄክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኃላ ቅደመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ገደበኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0113360631/146 ደደውሉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ
