ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ የህትመት ወረቀቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ የህትመት ወረቀቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ማስታወቂያ ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንደዚሁም ከሚያቀርቡት የወረቀት አይነት ለተግባር ሙከራ በቂ የሆነ ናሙና አብረው ያቀርባሉ፡፡
- ጨረታው ተከፍቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ያመጣው ናሙና ተሞክሮ ጥራት ካለፈ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው ወረቀቱን በሙሉ ቢዘገይ በ1 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር .........01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ.........0115 51 86 96
ፓ.ሳ.ቁጥር ...2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
