ድርጅታችን ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ እና በለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ የሚገኙትን የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን ያገለገሉ 100 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ከ113 ተሳቢዎች ጋር በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ
ድርጅታችን ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ እና በለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ የሚገኙትን የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን ያገለገሉ 100 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ከ113 ተሳቢዎች ጋር በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የጠቅላላ ዋጋውን 25% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች የእያንዳንዱን ዋጋ በግልጽ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 30 የሥራ ቀናት ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ ስልክ 251114-42-19-28/0930-30-41-10 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0935-98-50-83/0946-43-93-94 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሰኔ 5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ሰኔ 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን አይነት እና ይዞታ ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ 3000 TPD ቅጥር ግቢ ውስጥ (79 ተሸከርካሪዎች እና 91 ተሳቢዎች)፣ በአዳማ (19 ተሽከርካሪዎች እና 19 ተሳቢዎች)፣ በአዲስ አበባ (1 ተሽከርካሪ እና 2 ተሳቢዎች) እና በለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ (1 ተሽከርካሪ እና 1 ተሳቢ) ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 20 የሥራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
ማሳሰቢያ-
- ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ.
