በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የአጥርና G+1 የጥበቃ ማማ ሥራ ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የአጥርና G+1 የጥበቃ ማማ ሥራ ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2017 ዓ.ም 8 ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- አስፈላጊው የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
- በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውዏ ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GAURANTEE) ወይም የክፍያ ማዘዣ (cpo) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ሥ/ሂዳት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለቱ ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በስም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋ/ን/አስ/ሥ/ሂደት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፤ የተጫራቾች አለመጎኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462128084
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
