ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ. የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የፋብሪካውን ጣራ ዕድሳት በጣራ ጥገና ስራ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
የመጋዘን ጣሪያ ጥገና ስራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆቡማማ/ግ009/17
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ. የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የፋብሪካውን ጣራ ዕድሳት በጣራ ጥገና ስራ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን በሟማላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በጣራ ጥገና ስራ ወይንም በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የጥገና ስራውን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጋዘን ጣሪያ ጥገና ስራ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን ከገዝዙ በኋላ እስከ ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላየተየግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት የሥራውን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ግንቦት 29/9/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ3 /ሶስስት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የሥራ ውል ተፈራርሞ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 442 37 24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር
