በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ ዋና ሥራ ሂደት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ በሆነው በጌዴኦ ዞን ኅብረት ሥራ ጽ/ቤት ISVCD-SE ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በይርጋ ጨፌ ወረዳ ጪቱ ቀበሌ የፍራፍሬ ማከማቻ ፣ ጽ/ቤት ፣ መፀዳጃ ቤት ፣ የዘበኛ ቤት እና አጥር ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮች በደረጃ GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
የግንባታ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ ዋና ሥራ ሂደት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ በሆነው በጌዴኦ ዞን ኅብረት ሥራ ጽ/ቤት ISVCD-SE ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በይርጋ ጨፌ ወረዳ ጪቱ ቀበሌ የፍራፍሬ ማከማቻ ፣ ጽ/ቤት ፣ መፀዳጃ ቤት ፣ የዘበኛ ቤት እና አጥር ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮች በደረጃ GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በመስኩ የተሠማራችሁ ተጫራቾች፣
- ደረጃቸው GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በሥራና ከተማ ልማት ኮንስትራከሽን ሚንስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የ2016 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ በክልሉ እና በዞናችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉና ውል ያቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፤
- የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል፡፡
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ለ21 ተከታታይ ቀን በኋላ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ120 (90+30) ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ እና በኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፤
- ጨረታው የሚገመገመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነው፡፡
- በእጅ የተሞላ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
