Tender Detail

Tender Details


ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የአንቲ ቫይረስ፤ የኔትዎርክ ደህንነት መቆጣጠሪያ (Firewall)፣ ዲጅታል ሳይንኤጅ /Floor standing digital signage/፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች፤ የመበየጃ ጄኔሬተሮች እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የአንቲ ቫይረስ፤ የኔትዎርክ ደህንነት መቆጣጠሪያ (Firewall) ዲጅታል ሳይንኤጅ /Floor standing digital signage/ የተለያዩ መለዋወጫዎች፤ የመበየጃ ጄኔሬተሮች እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

 

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ቀን

ሎት 1

አንቲቫይረስ

50,000.00

15 ቀን

ሎት 2

የኔትወርክ ደህንነት መቆጣጠሪያ (Firewall)

50,000.00

30 ቀን

ሎት 3

ዲጅታል ሳይንኤጅ /Floor standing digital signage/

30,000.00

30 ቀን

ሎት 4

የተለያዩ መለዋወጫዎች

100,000.00

45-60 ቀን

ሎት 5

የመበየጃ ጄኔሬተሮች Welding Generators/

50,000.00

ከስቶክ

ሎት 6

ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች

100,000.00

45-60 ቀን

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል። የተጫራቾች መመሪያ፤

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና TIN ሰርተፍኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ከቀኑ 900 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 930 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው /ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ CPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
  7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሃሴ /2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ 90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
  11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው /ቤት መሆን አለበት።
  13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 058-220-4826/058-320-2548/ በፋክስ ቁጥራችን 058 220 4830 መጠየቅ ይችላሉ።

 

Save Tender