በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር -ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ 27/17
በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
- ምድብ 1 የዲያሌስስ ማሽን ግዥ
- ምድብ 2 የእሳት አደጋ ማጥፊያ ሙሌትና ጥገና ስራ ግዥ
- ምድብ 3 የጥበቃ አገልግሎት አውትሶርስ ስራ ግዥ ለአንድ ዓመት
- ምድብ 4 የፅዳት አግልግሎት አውትሶርስ ስራ ግዥ ለአንድ ዓመት
- ምድብ 5 ያገለገሉ እቃዎች አልሙኒየም በርና መስኮቶች ፣ የብረታብረት በርና መስኮቶች እና የተለያዩ እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት መስፈርቶችን አሟልታችሁ በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለጥበቃ ስራ ከፌዴራል ፖሊስ የሚሰጠው የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣ እንዲሁም የፅዳት አገልግሎት ስራ ልምድ ከመንግስታዊ ድርጅቶች ሁለት አመትና ከዚያ በላይ የሰሩበት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ ሰርተፍኬት ያላቸው
- አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1- 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሎት ስለሆነ ሙሉ በሙሉ በመሙላት መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሆስፒታሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ አፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3205738/058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባህር- ዳር
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
