የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለሚያካሄዳቸው የፕሮጀክቶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የተሸከርካሪዎች ዓይነት አቅራቢዎችን አወዳደሮ ከአሸናፊ ድርጅት ጋር የመኪና ኪራይ ውል መግባት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ECO-46/2017
የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለሚያካሄዳቸው የፕሮጀክቶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የተሸከርካሪዎች ዓይነት አቅራቢዎችን አወዳደሮ ከአሸናፊ ድርጅት ጋር የመኪና ኪራይ ውል መግባት ይፈልጋል።
- አነስተኛ የመስክ ተሽከርካሪዎች
- አነስተኛና መለስተኛ አውቶቡስ
- አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች
ስለሆነም በዚህ ጨረታ መካፈል የሚፈልጉ በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላትመሳተፍ ይችላሉ።
- ህጋዊና የዘመኑ ግብር የተገበረበት በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የቫትና የቲን ተመዝጋቢነት ማስረጃ የሚያቀርቡ
- የታክስና የተከፋይ ግብር በመክፈል ጨረታ ውስጥ የሚያሳተፋቸው ከገቢዎችና ጉምሩከ መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ታከስ ኪሊራንስ) ያላቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid BOND) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ) ማቅረብ ይኖርበታል።
- ከዚህ ቀደም አገልግሎት ከሰጡባቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርቶች ስለድርጅታቸውን ብቃትና ታማኝነት የተሰጣቸውን የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጨራቾች ዝርዝር የጨረታ መመሪያ (ሰነድ) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከድርጅቱ 3ኛ ፎቅ በመግዛት የጨረታ ሰነዳቸውን ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ወይም በዕለቱ በግንባር በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ በአራት ቅጂ በኦሪጂናልና በኮፒ እንዲሁም በቴክኒካልና በፋይናንስ ተሰርቶ በታሸገ ኤንቬሎፕ መቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታ ሰኔ 17, 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አደራሽ ውስጥ በግልጽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝና የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅታችን አድራሻ፡- ቃሊቲ የመካኒኮችን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊትለፊት ሲሲአርዲኤ አጠገብ የሚገኘው የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 3ኛ ፎቅ ላይ
ስልክ ቁጥር ፡- +251 11439 10 57 ፖሳ.ቁ. 870/250
ፋክስ 011 439 20 08
የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
