በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ SOLAR POWER SOLUTION SUPPLY, INSTALLATION, COMISSIONING, TRAINING and SUPPORT: Secure UV Printer. Security Ink ፣ ፋርጎ ላምኔሽን ፣ ፋርጎ ሪቨን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ግልጽ ጨረታ 3/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ SOLAR POWER SOLUTION SUPPLY, INSTALLATION, COMISSIONING, TRAINING and SUPPORT: Secure UV Printer. Security Ink ፣ ፋርጎ ላምኔሽን ፣ ፋርጎ ሪቨን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- ተጫራቶች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዕቃ አቅራቢነት ሊስት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ8/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመ/ቤታችን ክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በየሎት ጨረታ ሰነድ ሽያጭ ላይ በሚገኘው መሰረት ማስያዝ ወይም ቢድ ቦንድ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነዶች ዋጋ የሰጡበትን መስሪያ ቤታችን በሚያዘጋጀው ሰነድ መሰረት አንድ አሪጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በድምሩ በሁለት ፖስታ ለየብቻ ታሽጐ ባዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ22/10/2017 ዓ.ም በ4:00 ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በመ/ቤቱ ሚኒ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን የተጠየቀበት ማቅረብ አለባቸው። ለማቅረብ አስቸጋሪ የሆኑትን ዕቃዎች በአካል ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ስልሳ የስራ ቀናት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የፋይናንሻል ዋጋ መሙላት የሚቻለው ተቋሙ ባዘጋጀው ሰነድ መሰረት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የዕቃ አይነት ለአንድ ዕቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአንድ ዕቃ ሁለት አይነት ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
ማሳሰቢያ-
የሚገዛው ዕቃ ዝርዝር ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በተዘጋጀው የዕቃ ዝርዝር መሰረት በእያንዳንዱ ተራ ቁጥር የምታቀርቡበትን የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ እንዲገለጽ እና ሰነድ ለመግዛት ስትመጡ ፍላሽ ይዛችሁ በመምጣት በሶፍት ኮፒ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
