በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮንስትራክሽን የኮንስትራክሽ ልማት ቢዝነስ አዲስ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር IPDC/CDB-NCB/PG-001/2017
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮንስትራክሽን የኮንስትራክሽ ልማት ቢዝነስ አዲስ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ለድርጅቶች የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የዘመኑ ግብር ክሊራንስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ማንኛውም ድርጅት የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮንስራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ ግዥ ንብረትና አቅርቦት አስተዳደር ክፍል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ፣ የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ፣ ንብረትና አቅርቦት አስተዳደር ክፍል ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2017 ዓ.ም ከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 በኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ቀበና ከኬንያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሀ ቤት ህንፃ 3ኛ ወለል
ስልክ ቁጥር +251 91 242 0961
የኮንስትራክሽ ልማት ቢዝነስ
