የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ የገበያ ማዕከል G+4 የእጅ ሞያ ብቻ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ የገበያ ማዕከል G+4 የእጅ ሞያ ብቻ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ተጫራቾች በጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በግንባታ ስራ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የግብር ክፍያ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- የዘመኑን 2017 ግብር የከፈለ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ኦርጂናል እና ኮፒውን በግልፅ ለይተው ማቅረብ አለባቸው።
- የግንባታ ፍቃድ BC ወይም GC 1ኛ - 5ኛ ደረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- ተጫራቾች ብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር /በCBE እና በCBO ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ቢል ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ቼክ /CPO/ ወይም የባንክ ዋስትና በአርባጉጉ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች ግንባታው የሚሰራበት ቦታ በአካል ከጎበኙ በኋላ መጎብኘታቸውን የሚያሳይ ደብዳቤ ከመስሪያቤታችን መውሰድ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡30-11፡00 በዋና ቢሯችን በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በመርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01 ቀበሌ ከአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ጨረታው የሚከፈትበትን ቀን 11ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደሪያ ሰነዳቸውን አስገብቶ ይታሸግና በዚሁ እለት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ሆኖም የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ማሳሳቢያ፡- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0921096880/0912934586/ 0920063165/ ደውሎ መረዳት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በአርሲ ዞን የአርባጉጉ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
