Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)
  • Address ቸርችል ጎዳና፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ, Phone: 0115172521
  • Websitehttps://www.ebc.et/about.aspx
  • Deadline15 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-07-15 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፕሮዳክሽን ግብዓት ዕቃዎች NCB 0014/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NCB-0014/2017

የፕሮዳከሽን ግብዓት ዕቃዎች NCB 0014/2017 ግዥ ጨረታ

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፕሮዳክሽን ግብዓት ዕቃዎች NCB 0014/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገበበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 10,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ፣ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋና የቴከኒክ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቮሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኮርፖሬሽኑ ዋናው /ቤት ሸጎሌ ጊቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 500 ተዘግቶ ከጠዋቱ 515 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው /ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል።
  6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011 517 2521 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

 

Save Tender