ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተለያዩ የመጸዳጃ ቤት እና የቢሮዎች ዕድሳት እንዲሁም አዲስ የመጸዳጃ ቤት እና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
የግንባታ እና የጥገና ሥራዎች የአገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆቡማማ ግ.ጨ 002/17
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተለያዩ የመጸዳጃ ቤት እና የቢሮዎች ዕድሳት እንዲሁም አዲስ የመጸዳጃ ቤት እና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጥገና እና ግንባታ ሥራዎችን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሠራውን ሥራ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን ከገዙ በኋላ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል.ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ ፒ ኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
- ጨረታው ሰኔ 30 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ3 /ሶስት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የሥራ ውል ተፈራርሞ ሥራውን መጀመርይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 442 37 24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረ ፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
