ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የከባድና የቀላል መኪና ባትሪዎች እና ከባድና የቀላል መኪና ስፔር ፓርቶች በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ
ሎት 1 የከባድና የቀላል መኪና ባትሪዎች እና
ሎት 2. ከባድና የቀላል መኪና ስፔር ፓርቶች በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ10:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሲፒኦ የሚዘጋጀው MENSCHEN FUR MENSCHEN በሚል ስም ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10 ቀናት ውሰጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከድርጅቱ ዋና ማስተባበሪያ መ/ቤት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምሰት/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- 15ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር
011 471 4006/ 011 471 4291/
011 471 4358 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት
