ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሁለት ተሽከርካሪ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሁለት ተሽከርካሪ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በግዥ ከፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ስልክ ቁጥር 0115 15 50 05/ 0115 51 88 72
ፋክስ 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
