Tender Detail

Tender Details


የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች የህትመት ስራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ስታወቂያ

 

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም የተለያዩ የኤሌክትሮኒ እና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች የህትመት ስራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳዳሩ ተጋብዘዋል።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ሊራንስ) ማቅረብ አለባቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማናቸውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው መውጣት አይችልም።
  6. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን እና በናሙና መሰረት አሟልቶ ላልቀረበ ማንኛውም ሁኔታዎች ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የተጫራቾች /የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO /ሲፒኦ/ ወይም የባን ዋስትና በአስተዳደሩ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 200 እስከ ቀኑ 1100 ድረስ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው 16ኛው የስራ ቀን 400 ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
  10. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጽ/መሳሪያዎች የጽዳት ዕቃዎች ናሙና /ሳምፕል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በአስተዳደሩ ንብረት ፍል ማስገባት እና ስለማስገባታቸው ለግዥ የሥራ ክፍል ገቢ የተደረገበትን ማሰረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል መሆን አለባቸው
  11. ተጫራቾች ለወረቀት የህትመት ሥራዎች አስተዳደሩ የሚያቀርበውን ናሙና መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የቴክኒ ፋይናንስ ሰነዶችን በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  13. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ከቀረበ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።እንዲሁም በአስተዳደሩ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት።
  14. አሸናፊ ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  15. ጨረታውን ንፎ በወቅቱ ውል ለማሰር ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች በጨረታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /ሲፒኦ/ ለአስተዳደሩ ገቢ ይደረጋል። በቀጣይም አስፈላጊው አሰተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል።
  16. አስተዳደሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

.

የግዥው አይነት

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን

ሎት 1

የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና የኔትወርክ ዕቃዎች

የግድሠማዋኦ ብግጨ/01/01/2018

200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ በር/

ሎት 2

የጽህፈት መሣሪያዎች

የግድሠማዋኦ ብግጨ/01/02/2018

200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ በር/

ሎት 3

የጽዳት ዕቃዎች

የግድሠማዋኦ ብግጨ/01/03/2018

150,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ በር/

ሎት 4

የህትመት ስራዎች

የግድሠማዋኦ ብግጨ/01/04/2018

100,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ በር/

 

አድራሻችን፡- አዲስ አበባ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም መገናኛ ሕዳሴ ንጻ ወረድ ብሎ

የአስተዳደሩ ዋና /ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 1 ፎቅ

ለበለጠ ማብራሪያ ስልከ ቁጥር +251-111-56-88-90

 

የግ ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

 

Save Tender