Tender Detail

Tender Details


ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አ.ማ የተሽከርካሪ የተቃጠሉ ዘይቶች እና የተለያዩ ፍላፖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/02/2018

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲ አ. የተሽከርካሪ የተቃጠሉ ዘይቶች እና የተለያዩ ፍላፖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ኢትዮጵያዊ የሆነ /የሆነች እና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው/ ያላት እና በማንኛም ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ወይም የተሰማራች
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12 ፎቅ ከጠዋቱ 230 እስከ 1100 በመምጣት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና መወዳደር ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ ወይም በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ እንዲሁም ያስያዙትን ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ እቃዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ማየት ይችላል።
  6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት አጠቃላይ ያሸነፉበትን እቃ ፍያ ሙሉ በሙሉ በመክፈል እቃውን ከጊቢ ማውጣት አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ 16ኛው ቀን 800 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 830 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  9. ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ ሞጆ ይገኛል
  10. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ድራሻ:- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12 ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስል ቁጥር 011-558-25-19

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ .

 

Save Tender