ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ Toilet ball ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል በማዕቀፍ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nominees P.L.C
የጨረታ ማስታወቂያ
(በድጋሚ የወጣ)
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ Toilet ball ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል በማዕቀፍ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የእቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በስም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም እቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2:00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጥ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሀምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈ ተጫራች የእቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-555 19 11
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
