የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ለ2018 ዓ/ም ለክለቡ ስፖርተኞችና ለኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ለ2018 ዓ/ም ለክለቡ ስፖርተኞችና ለኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት:-
ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወደደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ መልኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለተመዘገቡ ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ/ ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ፋይናንስ ቢሮ አርተፊሻል ሜዳ ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጃ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ ለሚጠየቁ ዕቃዎች ናሙና የጨረታው ሰነድ በሚገባ ቀን ለእያንዳንዱ እቃዎቹ ላይ ኮድ በመስጠት በጨረታው አከፋፈት ሥነስርዓት ላይ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-212-4176
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ
