በማ/ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል lot one እስቴሽነሪ፣ lot two የሞተር ጎማ lot three የጽዳት እቃዎች፣ lot four ደረጃውን የጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ /01/
በማ/ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል lot one እስቴሽነሪ፣ lot two የሞተር ጎማ lot three የጽዳት እቃዎች፣ lot four ደረጃውን የጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በየንግድ ዘርፉ የተሰማራችሁ ተወዳዳሪዎች የዘመኑ ግብር የከፈላችሁበት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉና ከዚህ በፊት በጨረታ ያልታገዳችሁ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታችሁ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎች ኦርጅናል ሰነድና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል እስከዚያ ድረስ የጨረታ ዶክመንታችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው የሚያበቃው የመጨረሻው ቀን ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 /ስምንት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያግድ ነገር የሌለ መሆኑን እየገለጽን ቀኑ በበአል/ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላላፋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እስቴሽነሪ /20000/ ሀያ ሺህ ብር፣ የሞተር ጎማ 5000 /አምስት ሺህ/፣ የጽዳት እቃ 10000 /አስር ሺህ/ ብር ደረጃውን የጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦንላይን የተመዘገባችሁ ብቻ በጨረታው የምትሳትፉ ሲሆን ከዚህ ውጭ የሚመጣ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0113310812/ 0113310254
በማ/ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን አስተዳደር የቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
