ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለጹትን የከብትና እና የዶሮ ተረፈ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EL-LS-2025-009
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለጹትን የከብትና እና የዶሮ ተረፈ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ (መለያ ኮድ) |
የምርቱ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) |
የምርት መረከቢያ ቦታ |
|
ሎት 1 |
የዶሮ ተረፈ ምርቶች (የዶሮ ጉሮሮ፤ መጫጫሪያ፤ ጉበት፤ ልብ መቋደሻ 1 ቆዳና አጥንት) እንዲሁም የዶሮ ፍግ |
100,000.00 |
ደብረዘይት ዶሮ ምርት ኦፕሬሽን |
|
ሎት 2 |
ከእርድ የሚወጣ የከብት ተረፈ ምርት (የበሬ እና የበግ ሆድ ዕቃ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች) |
100,000.00 |
ደብረዘይት ኤክስፖርት ቄራ |
|
ሎት 3 |
ከእርድ የሚወጣ የከብት ተረፈምርት (የበሬ ሆድ ዕቃና ሌሎች ተረፈ ምርቶች) |
100,000.00 |
ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ |
|
ሎት 4 |
ከእርድ የሚወጣ የከብት ተረፈምርት (የበሬ ሆድ ዕቃ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች) |
100,000.00 |
መልጌ ወንዶ ምግብ ማቀነባበሪያ |
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
-
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ወይም የቲ.ኦ.ቲ. ተመዝጋቢ የሆኑ መጫረት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች አዲስ አበባ ላይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ - ሰነዱን ከጉርድ ሾላ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ ፤ የጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ነው።
- ተጫራቾች በገዙት ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው መሠረት መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም።
- ማንኛውም ተጫራች ለተረፈ ምርቱ ሲወዳደር ከላይ በሰንጠረዡ የተገለፀውን ብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርበታል።
- ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹትን ፎርማሊቲዎች በማሟላት በዚሁ ፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፖስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ለ 5 (አምስት) ቀናት በኤልፎራ ዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ገበያና ሽያጭ አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያስገቡ ይደረግና፤ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል፡፡ ከዚያም በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- +251911172601 +251 954495363
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር
