የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጨረታ ቁጥር 001 የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ ለመከራየት ስለፈለገ ከታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጨረታ ቁጥር 001 የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ ለመከራየት ስለፈለገ ከታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ መከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
Description(manufacture) |
Quality |
|
1 |
Production year 2016 pick up minimum capacity 2.4 L D4D Turbo charger |
4 |
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች
- በ2017 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት ምዝገባ፣ እና ከገቢ ግብር እዳ ነጻ ማስረጃ ጨረታው እስከሚገባበት ቀን የሚያገለግል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ዲሪ-ማሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀከት ከሚገኘው የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ በእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ተሽከርካሪ በመግለጽ ከተዛማጅ ማስረጃውን ሁሉንም ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም፡፡
- ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር በማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4:30 በግዢ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ፡– ዲሪ‐ማሻ መንገድ ፕሮጀክት የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ስልክ ቁጥር 0910009079
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
