የከሚሴ ማረ/ቤት መምሪያ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥሬ እህሎች፣ ሸቀጣሸቀጦች፣ የማገዶ እንጨት፣ በርበሬና ቅመማ ቅመም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ኮንትራት መስጠት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የከሚሴ ማረ/ቤት መምሪያ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥሬ እህሎች፣ ሸቀጣሸቀጦች፣ የማገዶ እንጨት፣ በርበሬና ቅመማ ቅመም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ኮንትራት መስጠት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ያለውን የምታሟሉ መጫረት ትችላላችሁ፡-
- አግባብ ያለው ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የምዝገባ የምስክር ወረቀት /ቲን/ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በማረ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 11 ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፣
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓት በማረ/ቤቱ ግቢ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። በዚያው እለት 5፡00 ሰዓት ይታሸጋል በ5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ማረ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት ወይም በስ/ቁጥር 0910755058 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
- ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የከሚሴ ማረ/ቤት መምሪያ
