የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል የማዕከሉን ግቢ የአጥር ግንባታና የዶሮ ቤት መስኮት ጥገና በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል የማዕከሉን ግቢ የአጥር ግንባታና የዶሮ ቤት መስኮት ጥገና በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ
1ኛ. የኮንስትራክሽን ንግድ ፈቃድ ያለውና ደረጃ BC/GC-7 /ሰባት/ እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
2ኛ. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፀም ስለመኖሩ የሚገልጽ ህጋዊ አሰሪ መ/ቤት ማቅረብ የሚችል፣ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል በማቅረብ አመሳክሮ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3ኛ. ተጫራች የተሟላ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ አንድ /1/ ኦርጅናል ሁለት /2/ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
4ኛ. ተጫራቾች በአርጅናሉ ፖስታ ውስጥ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ CPO የተያዘበት ሰነድ ገብቶ መታሸግ አለበት፡፡
5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
6ኛ. ተጫራቾች የጨታውን ዝርዝር ሰነድ በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000029079987 በኩል የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል መግዛት ይችላሉ።
7ኛ. የጨረታ አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
8ኛ. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ22ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በኩል ይከፈታል።
9ኛ. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወደም በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የመዝጊያና መክፈቻ ቀን ይሆናል፡፡
10ኛ. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
11ኛ. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማንኛውም ኦርጅናል መረጃ ላይ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
12ኛ. የጨረታው አሸናፊዎች በ7 ቀናት ውስጥ ውል ገብተው ሥራውን መጀመር ይጠበቅባቸዋል፡፡
13ኛ. ማዕከሉ ተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0473310841 ወይም 0934449883 ላይ ደውለው ይጠይቁ::
የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል
