የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ 12 ሰው የሚጭን አዲስ ያልተነዳ የህዝብ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመኪና ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ 12 ሰው የሚጭን አዲስ ያልተነዳ የህዝብ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የኤሌክትሪክ መኪና መሸጥ እና ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በይነ መረብ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ጽ/ቤት በአካል በመገኘት የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (200) ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዶችን በተናጥል በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በአካዳሚው የአስተዳደር እና ፋይናንስ ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አካዳሚው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0112570930 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡-
ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ወደ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አልፎ በቀኝ በኩል በሚታጠፈው መንገድ 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ
