Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግልጽ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/001/2018 የጄኔሬተር /Generator/ አቅርቦት፣ ገጠማ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ (Supply, installation, testing and Commissioning) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግልጽ ጨረታ ቁጥር /////001/2018 የጄኔሬተር /Generator/ አቅርቦት፣ ገጠማ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ (Supply, installation, testing and Commissioning) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ 2017/2018 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት / የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ ማስረጃቸውን ኮፒና ኦሪጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ /ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4 ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 700,000.00 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ነሃሴ 5 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9 ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ /ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ህንፃ

ስልክ ቁጥር 0936 99 35 20/ 0911 36 97 83

 

በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

 

Save Tender