Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Construction Works Corporation (የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን) (ሲኮስኮ)
  • Address ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ፊት ለፊት : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916071539
  • Website
  • Deadline16 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-08-17 00:00:00
  • Categories Vehicle

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለሥራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና (Dump Truck) እና ፍላት ትራክ (Flat Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 03/2017

 

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለሥራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና (Dump Truck) እና ፍላት ትራክ (Flat Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራ በዘርፉ ተገቢ የሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የአቅራቢነት የታደሰ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው።
  2. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎችና ከጉምሩ ፍቃድ ያላቸው
  4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነድ የሚሽጥበት ጊዜና ቦታ፡-

  1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፣

ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከቀኑ 830 እስከ 1100 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
  2. በማግስቱ 17ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  3. ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል

የጨረታ ዋስትና፡-

  1. ማንኛዉም ተጫራች 2% በባንከ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ የልዩ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የታ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶክሜንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916071539 ደው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ሲኮስኮ)

 

 

Save Tender