የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የላብቶሪ ሪኤጀንቶችንና ሳፕላይስ እንዲሁም የተለያዩ የህትመት ሥራዎችን ከሚመለከታቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ 005/18
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የላብቶሪ ሪኤጀንቶችንና ሳፕላይስ እንዲሁም የተለያዩ የህትመት ሥራዎችን ከሚመለከታቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች፡-
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ ሰርቴፊኬት ያላቸው
- አጠቃላይ የግዢ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ አቅራቢው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1- 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው የህትመት ሥራው ላይ ሙሉ በሙሉ መወዳደር ያለባቸው ሲሆን ሥራውን አሸናፊ የሆነው ድርጅት ለአንድ አመት ውል በመውሰድ ሆስፒታሉ በሚፈለገው ጊዜ በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ መሰረት ሠርቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በላብራቶሪ ራ-ኤጀንትና ሰፕላይስ ላይ ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገ/ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት የላብራቶሪ ሪኤጀንት ማንኛውንም ግብር እና ታክስ ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ እና ለህትመት ሥራው 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ/፣ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 /ዘጠኝ/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3205738 / 058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባህር ዳር
