የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሀይብሪድ ተሸከርካሪ ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (NCB017/2017)
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሀይብሪድ ተሸከርካሪ ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊና የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስከር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ሸጎሌ በሚገኘው በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክየተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲን ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከኦሪጅናል የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን የመወዳደሪያ ሰነዶች ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማህተማቸውን በመምታት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ6ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰኣት ድረስ ብቻ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከ8 15 ሰኣት በኋላ ማለትም የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸጎሌ በሚገኘ በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ውስጥ ይክፈል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸጎሌ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-517-25-11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
