በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የወራቤ ስቴዲያም ትሪቡን ግንባታ ለማስገንባት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የወራቤ ስቴዲያም ትሪቡን ግንባታ ለማስገንባት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ደረጃቸው G.C-5 /B.C-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፣
- የጨረታ ዋስትና 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፣
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ሥራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር03 በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠቀሰው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጡም።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0467710586 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
