የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር አ/አ/ከ/አስ/ዲ/ግ/ሥ/ቢሮ 001/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለመስጠት በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን አሟልቶ ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት አለት አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ ቢ.ቁጥር 11-04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ /ሲፒኦ/ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ተመላሽ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በሰባተኛው ቀን አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- 6 ኪሎ አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ህንጻ ላይ ስ.ቁጥር፡- 011 154 1475/011 154 19 12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
