አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AMFI 01/2017/18
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ምድብ 1፡- ጀነሬተር
ምድብ 2፡- ኮምፒዩተር እና ፕሪንተር
ምድብ 3፡- የጽ/መሣሪያዎች
ምድብ 4፡- የጽዳት እቃዎች
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ
- ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምድብ 1 የሚቀርብ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 2፡3 እና 4 የሚቀርብ ለእያንዳንዳቸው 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ለምድብ 1 እና 2 ከጠዋቱ 3፡00 (ሦስት ሰዓት) ድረስ እና ለምድብ 3 እና 4 ከቀኑ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ምድብ 1 እና 2 ከጠዋቱ 3፡00 (ሦስት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 3፡30 (ሦስት ሰዓት ተኩል) ላይ እና ምድብ 3 እና 4 ከጠዋቱ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 5፡30 (አምስት ሰዓት ተኩል) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያእቆብ ሕንፃ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 637 66 68/011 637 64 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
