በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታል መገልገያ የሚሆኑ ተኝተው ለሚታከሙ እና ለተረኛ የጤና ባለሙያ የምግብ አቅርቦት፤ ህትመት፤ የመኪና ጥገና እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ዓመታዊ ውል፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/ 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታል መገልገያ የሚሆኑ ተኝተው ለሚታከሙ እና ለተረኛ የጤና ባለሙያ የምግብ አቅርቦት፤ ህትመት፤ የመኪና ጥገና እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ዓመታዊ ውል፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፈል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
ሎት 1. ተኝተው ለሚታከሙ እና ለተረኛ የጤና ባለሙያ የምግብ አቅርቦት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ ብር/
ሎት 2. የመኪኖች ጥገና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ ብር/
ሎት 3. የህትመት ሥራዎች እና ቲተር ብር 15,000.00 / አስራ አምስት ሺ ብር/
ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO "ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል" ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኅተምና ፊርማ እኑረው ፋይናሻል እና ቴክኒካል ኮፒ ለብቻ ፋይናሺያል ኦርጅናል ለብቻ ቴክኒካል ኮፒ ለብቻ በድምሩ 3 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 - 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- አሽናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ - ስልክ 0924777840 በስራ ሰአት መደወል ይችላል፡፡
የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል
