በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሣሪያዎች፤ የተለያዩ ማሽን ቀለሞች እና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2017-2018
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 የተለያዩ ማሽን ቀለሞች
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግዢው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፤ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር መያያዝ አለበት፣
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሣሪያዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/፣ ለተለያዩ ማሽን ቀለሞች ብር 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/፣ ለፅዳት ዕቃ 25,000 /ሃያ አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO፣ ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃlን።
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
