ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ የተለዩዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎችን ሕጋዊ ከሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04 እና 05/24/25
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ የተለዩዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎችን ሕጋዊ ከሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀምርባ) ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የድርጅታቸውን የመስመር ስልክ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ አድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ለጽህፈት መሳሪያ እና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ለተሽከርካሪ ጎማ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማስያዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ 8፡15 ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 12 04 ወይም 011 531 80 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
