የደ/ም/አ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም ለፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያገለግል HI-Tec Computer, Laptop computer, Desktop compter, Printer በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ም/አ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም ለፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያገለግል HI-Tec Computer, Laptop computer, Desktop compter, Printer በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራች:-
1ኛ. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የ2017 ዓ/ም ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2ኛ. ተጫራቾች የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ የሆነና፤ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3ኛ. ተጫራች ከዚህ በፊት በዘርፉ ዕቃ ያቀረበበት ሕጋዊ ሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4ኛ. ተጫራች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
5ኛ. ተጫራች በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ሰነዶች ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለብቻ ፖስታ በሰም በማሸግ፡ እንዲሁም ቢሮው ባዘጋጀው ጨረታ ሠነድ ላይ በሚነበብ ጽሑፍ በሙሙላት የድርጅቱን ስም ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በማቅረብ ለዚሁ ጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባችኋል።
6ኛ. ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ጨረታው አየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ፣ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጧቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
7ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ስትሞሉ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት። ካልሆነ ውድቅ ይደርጋል።
8ኛ. ተጫራቾች አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዕቃ ዋጋ 10% CPO በኮሚሽኑ ሥም በማስያዝ በ3 ቀን ውስጥ ውል መግባት አለበት።
9ኛ. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በታርጫ ከተማ ድረስ ማስገባት አለበት።
10ኛ. ተጫራች ጨረታ በሚከፈት ጊዜ በእስፔስፊኬሽኑ መሠረት የተጠየቁ ዕቃዎች ከእያንዳንዱ አንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
11ኛ. ተጫራች ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም ።
12ኛ. ተጫራች የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
13ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በመ/ቤቱ ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ CPO /ጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14ኛ. ተጫራች የባንክ ጋራንት ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም።
15ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት 1000521691305 ላይ ገቢ በማድረግ ባንክ አድቫይስ ስታመጡ በ/ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ርዳይሬክቶሬት በታርጫ ከተማ ከቴሌ ቢሮ በስተጀርባ በሚገኘው ቢሮ በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ።
16ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
