Tender Detail

Tender Details


በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ከ/መንግስት የኮንታ ዞን በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በሎትı ጽ/መሣሪያ፣ በሎት2 ኤሌከትሮኒከስ፣ በሎት3 ኮንታ ብሔር ባህል አልባሳት፣ በሎት4 ሞተርሳይከል እና በሎት5 የቪዲዮ ካሜራ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ከ/መንግስት የኮንታ ዞን በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በሎትı ጽ/መሣሪያ፣ በሎት2 ኤሌከትሮኒከስ፣ በሎት3 ኮንታ ብሔር ባህል አልባሳት፣ በሎት4 ሞተርሳይከል እና በሎት5 የቪዲዮ ካሜራ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

1/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ 2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት 3/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)፤ 4/ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ 5/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት እና 6/ የመልካም ሥራ አፈፃፀም በየዘርፉ የ2016 ወይም 2017 ዓ.ም ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣ በ2018 በጀት ዓመት ፈቃድ ያወጡትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም አይመለከትም፡፡

7/ ተጫራቾች ለሎት፡ እና ለሎት2 የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሲሆን በሎት3 እና በሎት4 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር እና ሎት5 20,000(ሃያ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8/ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 15ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ የጨረታ ዶከመንት በመግዛት እና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴከኒካል አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 4 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9/ በተራ ቁጥር 8 መሠረት የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው በ16ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ ይከፈታል፡፡

10/ ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመከፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 9 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11/ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል በመግባት ንብረቱን እስከ ኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አመያ ከተማ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

12. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፁትን መስፈርቶችን የማያሟላ ተጫራች ለቴከኒካል ግምገማ አይቀርብም፡፡

13/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0917388691/0917161785 ወይም 0910262925

አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ሕ/ ከ/ መንግስት ኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጅማ ከተማ በስተ ደቡብ 102 ኪ.ሜ በአመያ ከተማ ይገኛል።

Save Tender