በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም የጽዳት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 893-02
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም የጽዳት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች፡-
1ኛ. የ2017 ዓ.ም ግብር የክፈሉ፣
2ኛ. በዘርፉ የወጽዓ ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
3ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፤
4ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5ኛ. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው።
6ኛ. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር ዘር አስር ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚችል።
7ኛ. የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ/ጽ/ቤት መግዛት የሚችል።
8ኛ. ተወዳዳሪዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት የሚችሉ።
9ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን እና የድርጅቱን ስም እና ማህተም በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው (16) ቀን 6፡00 ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10ኛ. ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰዓት ገብቶ ካለቀ በኋላ በእለቱ 6:30 ሰዓት (ስድስት ሰዓት ተኩል ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8 ሰዓት (ስምንት ሰዓት) በጉ/ወ/ገ/ጽቤት ይከፈታል።
11ኛ. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽህፈት ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ ዋስትና ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
12ኛ. እዚህ ማስታወቂያ ላይ ያልተጠቀሱ መስፈርቶችን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251967671200 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
