የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሚያከናውነው የመንገድ ስራ ሎት 1 (አንድ) ለፓይፕ ማምረቻ የሚውል የፓይፕ ሞልድ፣ ሎት 2 (ሁለት) ኮንክሪት ሚክሰር እና ኮንከሪት ቫይብሬተር፣ ሎት 3 (ሶስት) ለተለያዩ የበርና መስኮት ሥራዎች የሚውሉ የፋብሪካ የብረት ውጤቶች በጨረታ ቁጥር ዲ/ማ/መ/ግ/ፕጨ -004 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሚያከናውነው የመንገድ ስራ ሎት 1 (አንድ) ለፓይፕ ማምረቻ የሚውል የፓይፕ ሞልድ፣ ሎት 2 (ሁለት) ኮንክሪት ሚክሰር እና ኮንከሪት ቫይብሬተር፣ ሎት 3 (ሶስት) ለተለያዩ የበርና መስኮት ሥራዎች የሚውሉ የፋብሪካ የብረት ውጤቶች በጨረታ ቁጥር ዲ/ማ/መ/ግ/ፕጨ -004 አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ ከታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ መግዛት
|
ተ/ቁ |
ዝርዝር |
ብዛት |
|
ሎት 1 - ፓይፕ ሞልድ |
||
|
1 |
Pipe Mold # 42 |
30 |
|
2 |
Pipe Mold # 48 |
10 |
|
ሎት 2 - ኮንክሪት ሚክሰር እና ኮንክሪት ቫይብሬተር |
||
|
1 |
Concrete Mixer #350 MI |
4 |
|
2 |
Concrete Mixer #750 MI |
3 |
|
3 |
Concrete Vibrator #3 MM |
4 |
|
ሎት 3- የተስያዩ የፋብሪካ የብረት ውጤቶች |
||
|
1 |
Sheet Metal: 1mx1mmx2m |
100 |
|
2 |
LTZ-Iron: 48 x 48 x 1.5 |
700 |
|
3 |
D-Iron: 30 x 20 |
400 |
|
4 |
RHS: 20×10×1 |
350 |
|
5 |
Grill |
300 |
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን ሁኔታ በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
1. በ 2017 ዓ.ም ለዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርወረቀት፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፤ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር፤ የአቅራቢነት ምዝገባ እና ከገቢ ግብር እዳ ነጻ ማስረጃ ጨረታው እስከሚገባበት ቀን የሚያገለግል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ዲሪ-ማሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከሚገኘው የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00 በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሎት በመግለጽ ተዛማጅ ማስረጃቸውን ሁሉንም ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጠን ውስጥ የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ጻጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም፡፡
5. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
6. የጨረታ ሳጥኑ ጻጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡ 30 ሰዓት በግዢ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡-09-10-00-90-79
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ‐ማሻ
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
