ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለዋናው መ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ የጨረታ ቁጥር- አመስደ 02/2018 ኅብር ኮንስትራከሽን ኮርፖሬሽን ለዋናው መ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
01 |
Cisco catalyst C9300-48P Network switch |
pcs |
02 |
|
02 |
Cisco catalyst C9300-24P Network switch |
pcs |
05 |
|
03 |
10,000VA APC Smart - Ups |
pcs |
02 |
|
04 |
Extra Hard disc |
pcs |
02 |
|
05 |
32 GB USB Flash |
pcs |
03 |
|
06 |
Full Copper Cat 6A UTP Network kable |
Roll (350m) |
305m (1) |
|
07 |
Industrial crimped Ethernet 5-meter Full Copper Cat 6A UTPP Network Cable |
Pcs |
50 |
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይንም በዘመኑ የተሰጠ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ተክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ተጫራቾች በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ ማለትም ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ቢጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ9:30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓላት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ኮርፖሬሽናችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የኔትወርክ ዕቃዎች ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንገልጻለን።
- ውድድሩ ከቫት ጋር በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው። ስለሆነም ሁሉም ተወዳዳሪዎች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች አንዱን ወይንም ከዚያ በላይ ያልሞላ ተወዳዳሪ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
