Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Construction Works Corporation (የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን) (ሲኮስኮ)
  • Address ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ፊት ለፊት : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916071539
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲሰ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Vehicle

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና(Dump Truck) እና ፍላት ትራክ (Flat Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ሲኮስኮ)

በድጋሚ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ቁጥር

05/2017

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና(Dump Truck) እና ፍላት ትራክ (Flat Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች በዘርፉ ተገቢ የሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

1. በዘርፉ አቅራቢነት የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው

2. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

3. በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎችና ከጉምሩክ ፍቃድ ያላቸው

4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል

የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፡-

1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር300/ሦስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፣

ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ ከ8፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡

2. በማግስቱ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

3. ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::

የጨረታ ዋስትና፦

1 ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነስ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ-

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የልዩ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነትና የታከስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተደገፈ /CPO/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶኩሜንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

2. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

 ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916071539 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ሲኮስኮ)

Save Tender