የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን ቃሊቲ ከሚገኝው ዋናው ቢሮ ወደ ተለያዩ ሳይቶች ከአቅራቢዎች ወደ ሳይትና ዋና ቢሮ የሚያጓጉዙ ተሸከርካሪዎች (ገልባጭ እና ፒካፕ) ኪራይ አገልግሎት ጨረታ ሰነዱ ላይ በሚቀመጠው መስፈርት መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/2/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን ቃሊቲ ከሚገኝው ዋናው ቢሮ ወደ ተለያዩ ሳይቶች ከአቅራቢዎች ወደ ሳይትና ዋና ቢሮ የሚያጓጉዙ ተሸከርካሪዎች (ገልባጭ እና ፒካፕ) ኪራይ አገልግሎት ጨረታ ሰነዱ ላይ በሚቀመጠው መስፈርት መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስስሆነም:-
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብርበመከፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሠልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የተሽከርካሪ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የፍላጎት መግለጫ (specification) መሰረት ድርጅታችን ባቋቋመው የቴከኒክ ኮሚቴ ወይም በሶስተኛ ወገን ሊታይ ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼከ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ላይ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
5. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 011-4-39-77-46 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራከሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
