የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት የተለያዩ ጥቅም ላይ የሚውሉ ያገለገሉ ዕቃዎችና ተረፈ ምርቶች፣ የህትመት ጥሬ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የሳይንስ ኪት ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የታይፕራይተር መለዋወጫዎች እና ሌሎች ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት የተለያዩ ጥቅም ላይ የሚውሉ ያገለገሉ ዕቃዎችና ተረፈ ምርቶች፣ የህትመት ጥሬ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የሳይንስ ኪት ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የታይፕራይተር መለዋወጫዎች እና ሌሎች ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
- የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሠርተፊኬት/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው ዝርዝሩን መመልከት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ፡-
- ሎት አንድ-የተለያዩ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፤
- ምድብ አንድ - NISANE
- ምድብ ሁለት - IVECO
- ምድብ ሶስት - Mercedes
- ምድብ አራት - የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ሎት ሁለት - የሳይንስ የትምህርት መርጃ ምርት ግብዓቶች እና ሌሎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)፤
- ሎት ሶስት - የተለያዩ የህትመት ማሽን መለዋወጫ፣ ጥሬ እቃዎች እና ተረፈ ምርቶች፤
- ምድብ አንድ - የህትመት ማሽን መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣
- ምድብ ሁለት - የህትመት ልዩ ልዩ ጥሬ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣
- ምድብ ሦስት - የህትመት ተረፈ ምርት ኮር ያለ ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣
- ቁርጥራጭ ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000፣
- ሲግኔቸር ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000፣
- ሎት አራት - ልዩ ልዩ የፈርኒቸር ምርት ግብዓቶች እና ሌሎች ዕቃዎች፤
- ምድብ አንድ - ልዩ ልዩ የፈርኒቸር እቃዎች (በተናጠል) የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- ምድብ ሁለት - ልዩ ልዩ የፈርኒቸር የእጅ መገልገያ መሣሪያዎች (በጥቅል) ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣
- ሎት አምስት - የታይፕ ራይተር መለዋወጫዎች (በጥቅል) የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣
- ሎት ስድስት - የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ እምስት ሺህ ብር)፤
- ሎት ሰባት - ንቃይ የታምቡራታ በሮች እና የበር ነጠላ መቃን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት ስምንት - ፓሊትሊን ባለ 25 ኪግ ብዛቱ 8,750 ኪ/ግራም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ ብር)፤
- ሎት ዘጠኝ - የተለያዩ የህትመት ዝርግና ጥቅል ወረቀቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤
- ሎት አስር - የተለያዩ የካሜራና የሕትመት ፊልሞችና ቀለሞች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፤
- ሎት አስራ አንድ - የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች (በጥቅል) የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋርበማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ንብረቶቹ በሚገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በሚገኘው መመልከት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ዝግ ላይ ከዋላ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የድርጅቱ አድራሻ፡- አ/አ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንፃ ወደ ቀኝ በ ILRI እና FAO ድርጅቶች መካከል በሚያስገባው መንገድ ላይ 100 ሜትር ወደ ውስጥ ገብቶ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በሥራ ሰዓት ፡- 011-6-46-09-61 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
