አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ቦሌ ክ/ከተማ ቱሪስት ሳይት ብሎክ 4 የቤት ቁጥር 208 እና ለሚኩራ ክ/ከተማ ብሎክ 3 የቤት ቁጥር 103 የሚገኙትን የንግድ ቤቶችን የፊኒሽንግ ስራዎች ሙሉ ማቴሪያሉን ተወዳዳሪዎች ችለው በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ያሉ ተወዳዳሪዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና በከተማዋ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አማካኝነት የማምረቻ መሳሪያዎችን ለጥቃቅንና አነስተኛና ታዳጊ ኢንተርፕራይዞች በካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን፡-
ቦሌ ክ/ከተማ ቱሪስት ሳይት ብሎክ 4 የቤት ቁጥር 208 እና ለሚኩራ ክ/ከተማ ብሎክ 3 የቤት ቁጥር 103 የሚገኙትን የንግድ ቤቶችን የፊኒሽንግ ስራዎች ሙሉ ማቴሪያሉን ተወዳዳሪዎች ችለው በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ያሉ ተወዳዳሪዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ የንግድ ቤት 30,000 (ሠላሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12/2018 ዓ.ም የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ከርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ ህንፃ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አርጅናልና ኮፒ በፖስታ ታሽጎ እስከ መስከረም 12/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 12/01/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከኩባንያው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ውጭ ዋጋ ሞልቶ መመለስ ከጨረታ ያሰርዛል፣
አድራሻ፡- ፒያሳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ ህንፃ ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-1-26-38-88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
