የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች (ከ3 ኢንች እስከ 24 ኢንች ወይም ከ88.3-609, ሚሊ ሜትር) የብረት ቧንቧዎችን በግምት 750 ቶን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለኮንስትራክሽን፣ ለመስኖ ውኃ ማስተላለፊያ፣ ለተለያየ ዓይነት
ፍሳሽ ማስወገጃና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ የብረት
ቧንቧዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች (ከ3 ኢንች እስከ 24 ኢንች ወይም ከ88.3-609, ሚሊ ሜትር) የብረት ቧንቧዎችን በግምት 750 ቶን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (መቶ ብር) በመክፈል ከኩባንያው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ በመውሰድ ይህ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም ወይም ቶን የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) በሲፒኦ ወይም ከባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ቦሌ መንገድ ቢትወደድ ባሕሩ አብርሃም ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ የብረት ቧንቧዎቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያችን ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል።
ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር: +251-5522681/+251-5522731
አዲስ አበባ
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
