የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች የሚያቀርብ በዘርፉ ከተሰማሩት ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በሚከተለው ዝርዝር ሰነድ ይጋብዛል
የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሰ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/003/2018
የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች የሚያቀርብ በዘርፉ ከተሰማሩት ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በሚከተለው ዝርዝር ሰነድ ይጋብዛል፡-
|
ሎት
|
የእቃው አይነት
|
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰአት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰአት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ
|
|
03
|
የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች
|
መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡ዐዐ ሰዓት ይዘጋል |
መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰአት ይከፈታል |
ብር 125,424.30.00 (አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺ አራት መቶ ሃያ አራት ብር ከ30/100) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር ያለው በጨረታ መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከተሰጣቸው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህንጻ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን 2ተኛ ፎቅ ግዢና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁ.ት 210 በመምጣት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት ዐ3 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-North AACC. (1000149984384) ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በማስገባት ይዞ ቀርቦ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለስድስት ወራት የሚያገለግል የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/003/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ፊት ለፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህንጻ ውስጥ 2ተኛ ፎቅ ሰፕላይ ቼይን እና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 210 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 251-11 171-5365 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን
አዲስ አበባ
